ተልዕኮ፣ አላማ፣ኢላማዎች (MISSION,PURPOSE,TARGETS)

↪ተልዕኮ

ወንጌልን ላልዳኑ ህዝቦች በሙሉ መስበክ።

↪ዓላማ

የፉል ፔንቴከስታል ቤተክርስቲያን ዓላማ
”ሰዎችን ከክርስቶስ ጋር በማስተዋወቅ ክርስቶስን በሙላት የሚያውቅ አርአያ ደቀመዛሙርትና አገልጋዮች በማድረግ እግዚአብሔርን ማክበር ነው፡፡”
🔎 ይህ አላማ የሚሳካው ክርስትያኖች በአምልኮ ፣በማስተማርና በህብረት ራሳቸውን እንዲያሳድጉና በህይወታቸው እንዲበስሉ በመርዳት ነው፡፡
↪ ዒላማ

የፉል ፔንቴከስታል ቤተክርስቲያን በወንጌል ለመድረስ ትኩረት ሰጥታ ለመስራት የታጠቀችው የሰዎች ዓይነት የሚከተሉት ናቸው፡-

🔎በተለያዪ አጋንንታዊ እስራት ውስጥ ያሉ ሰዎች፣

🔎በየሆስፒታሉ ታመው የተኙ ሰዎች፣

🔎የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣

🔎ሁኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ፣

🔎 አእምሮ ህሙማን፣

🔎ጎዳና ተዳዳሪዎች

🔎 ሴተኛ አዳሪዎች

የፉል ፔንቴከስታል ቤተክርስቲያን በወንጌል ለመድረስ ትኩረት ሰጥታ በወንጌል ለመድረስ ያቀደችው ሀገራት ኢትዮጽያ፣አፍሪቃ፣ኤስያ፣አውሮፓ፣አሜሪካ፣ቻይና ናቸው።

የፉል ፔንቴኮስታል ቤተክርስትያን
የፉል ፔንቴኮስታል ቤ/ክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል 28፡18 እንዳዘዘው ታላቁ ትእዛዝ ይህም

” ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል ስለዚህ ሂዱና ህዝባችን ሁሉ በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቅኋችሁ ደቀመዛሙርት አድርጓቸው የያዝኋችሁ ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው ”

፤በሚለው ቃል መሰረት ቤተክርስቲያናችን ይህን ታላቁን ተልእኮ ከግብ ለማድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ተካይ እና የአገልግሎቱ መሪ ነብይ መሳይ አለማየሁ ላለፉት ሶስት አመታት ከአብሮ ሰራተኞች ጋር ሲጸልዩ እና ሲዘጋጁ ከቆዩ በኋላ በእግዚአብሄር መንፈስ እና ፀጋ ቤተክርስቲያናችን ይፋዊ አገልግሎቷን ለመጀመር በቅታለች፤ ለዚህም የረዳንን ጌታ አማላካችን እግዚአብሔርን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፡፡

ቤተክርስቲያናችን እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ለአለም ህዝቦች ሁሉ ዘላለማዊ አጀንዳ አስፈጻሚ ነች፡፡ ይህ እውን ይሆን ዘንድ ታላቁን ተልእኮ ወንጌል በመሰበክ በማስማር ፤ ደቀመዝሙር በማድረግ መፈፀም እንዲሁም ሰዎች የጌታ ደቀመዛሙርት ማድረግ ይቻል ዘንድ በቤተክርስቲያን አነስተኛ ቡድኖች (የእድገት ደረጃዎች) በመያዝ በማስተማር እና በመንከባከብ ከዚያም ወደ ብስለት ደረጃ ማምጣት፤ቤተክርስቲያናችን ሰዎችን ለእግዚአብሄር መንግስት በቁ በማድረግ የአገልግሎት ትምህርት ማስተማር ፤ማሰልጠን እና ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸውን የአገልግሎት ፀጋ በመለየት በፀጋ ስጦታቸው ወደ አገልግሎት ማሰማራት ለአገልግሎታቸው ዕውቅና ሰጥቶ የእግዚአብሔርን መንግስት ማገልገል ሌላው የቤተክርስትያን ተግባር ነው፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ የዳነና የቤተክርስቲያናችን አባል የሆነ ሰው ሁሉ በሚከተሉት መንገዶች አስፈላጊውን መንፈሳዊ እንክብካቤ ያኛል፤

የተለያየ መንፈሳዊ ደረጃ ባላቸው የአነስተኛ ቡድን ውስጥ በመሆን ክትትል /እንክብካቤ ያገኛል፤

አስፈላጊው ጉብኝት ይደረግለታል (በቤተሰብ ፤ስራ ቦታ እና በተሰማራበት ጎዳና)፤

አስፈላጊው የምክር አገልግሎት ይደረግለታል

በግል የፀሎት አገልግሎት ያገኛል

ቅርበት ያለው ግንኙነት በአካል ወይም በስልክ ያገኛል፤

↪በመንፈሳዊ ህይወቱ፣በቤተሰብ ህይወቱ፣በማህበራዊ ህይወቱ የበሰለ ህይወት ይመራል፤

በመንፈሳዊ ህይወት ብቁ ሆን ዘንድ ይማራል ፤ህብረት እና አምልኮ ያደርጋል፤

ለአገልግሎት ስራ ብቁ ይሆናል፤

የፉል ፔንቴከስታል ቤተክርስቲያን የአምልኮ ፤የክርስቲያናዊ ትምህርት እና የህይወት ተዛምዶ ሚዛን ትጠብቃለች ፤ጥሩ እና የተሻለ ህብረት እለት ተእለት በአማኞች ህይወት ውስጥ ለመገንባት ትተጋለች መሰረታዊ የክርስቲያን ትምህርት ትሰጣለች ወደ ብስለት የሚደርሱ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥምህርቶችንም ታካትታለች ፤የወንጌል ስርጭት ታካሂዳለች፡፡

ዘርፈ ብዙ በሆኑ ሰዎች ታቅፋለች እነዚህ የተለያየ ደረጃ ላቸው የት/ት ደረጃዎች ሲሆኑ በመቀጠልም ቤተክርስትያናችን ታላቁን ተልእኮ ለመፈፀም ራእይዋን ከግብ ለማድረስ ይፋዊ አገልግሎቷን በ2011ዓ/ም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጀምራለች፡፡

ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ፤የእግዚአብሔር ፍቅር ፤ የመንፈስ ቅዱስ ህብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን አሜን !!

የዓላማ መግለጫ

የፉል ፔንቴኮስታል ቤተክርስቲያን ያለን ዓላማ ሰዎችን ከክርስቶስ ጋር በማስተዋወቅ ክርስቶስ በሙላት የሚያውቅ አርአያ ደቀመዛሙርትን በማድረግ እግዚአብሔርን ማክበር ነው፡፡

ይህ አላማ የሚሳካው በአምልኮ በማስተማርና በህብረት ራሳቸውን እንዲያሳድጉና በህይወታቸው እንዲበስሉ በመርዳትነው፡፡

አስተምህሮ መግለጫ

የፉል ፔንቴኮስታል ቤተክርስቲያን የአስተምህሮ መግለጫ እንደሚከተለው ነው፡-

የእግዚአብሔር ቃል ፡- መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነና ሙሉ በሙሉ እስትናፋሰ- ቃል እንደሆነና መጀመሪያ በተፃፈበት ሁኔታ ምንም ስህተት በሌለበትና በህይወት እና ለእምነት የመጨረሻ ስልጣን ያለው መሆኑን እናምናለን፡፡

ሥላሴ፡- አንድ ህያውና እውነተኛ አምላክ ዘላለማዊና በሶስት አካላት ያለ፤ እነዚህም በሁሉም መለኮታዊ ፍጽምና እኩል ሲሆኑ ለማዳን እና በመዋጀት ስራ እያንዳንዳቸው የተለያዩ ተግባር ቢኖራቸውም ይህንን በስምምት እንደሚያከናውኑ እናምናለን፡፡

እግዚአብሔር አብ፡- ሕያው በሆነ ወሰን በሌለው የራሱ ማግንነት ባለው መንፈስ በቅድስናው ፤በጥበብ በሀይልና በፍቅር ፍጽም በሆነ አምላክ እናምናለን ፤ የእያንዳንዱ ሰው ህይወት በፍቅር እንደሚመለከት ፤ፀሎት እንደሚሰማና እንደሚመለስ ፤እሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ እርሱ የሚመጡትን ሰዎች ሁሉ ከሀጢትና ከሞት እንደሚያድን እናናለን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ፡- የእግዚአብሄር አንድያ ልጅ ከሆነውና በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰው ክርስቶስ በተአምእራና በትምህርቱ እናምናለን ፡፡ ከድንግል መወለዱን፤ ኃጢያት የሌለበት መሆኑን እንዲሁም በተአምራቱና በትምህርቱ እናምናለን፡፡ለሀጢያታችን ምትካችን ሆኖ መሞቱንና ከሞትም በአካል መነሳቱን ወደ ሰማይ መረጉን ፤ የማያቋርጥ ምልጃ በህዝቡ እንደሚያደርግና በግልፅ ወደ ምድር ተመልሶ እንደሚመታ እናምናለን፡፡

መንፈስ ቅዱስ፡- መንፈስ ቅዱስ የስላሴ አንዱ አካል ሆኖ ከአብና ከወልድ ወጥቶ በወጣው ኣለምን ስለ ሀጢት ስለፅድቅና ስለ ፍርድ የሚወቅስ ዳግመኛ ልደትን ሊሰጥ ሊቀድስና ለኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑትን ሁሉ በኃይል በሚሞላው መንፈስ ቅዱስ እናምናለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ባመኑ አማኞች ሁሉ ውስጥ እንደሚኖር ረዳት አስተማሪ እና መሪ፣አፅናኝ፣መካሪ፣ለአገልግሎት እንደሚለይ እናምናለን፡፡

ዳግም ልደት፡- ሁሉም ሰዎች በፍጥረታቸው በምርጫቸው ኃጢአተኛ እንደሆኑና በፍርድ ስር እንደሆኑ እናምናለን ፡፡ ስለሀጢያታቸው ንስሃ የሚገቡና ኢየሱስ ክርስቶስ በአዳኝነቱ የሚምኑ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ዳግመኛ እንደሚወለዱ እናምናለን፡፡

ቤተክርስቲያን፡– በአንዲት ዓለም አቀፍ ራሷ ክርስቶስ የሆነ ሕያውን መንፈሳዊ አካል በሆነች ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ሁሉ አባሎቹ በሆኑት ቤተክርስቲያን እንምናለን፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ያኑ ሰዎች ህብረት ባለበት አሳማኝ በሆነ ንስሃ የተጠመቁ ለአምልኮ ለስራና ለህብረት በሚሰበሰቡበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን እናናለን፤ በጠፋው አለም አለም የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማድረስ ቅድሚ ኃላፊነት በአጥቢ ቤተክርስቲን አባላት እንደተሰጠው እናምናለን፡፡

ክርስቲያናዊ ባህሪይ ፡- ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር ክብርና ለሌሎችም ጥቅም መኖር እንዳለባቸው እናምናለን፡፡ ባህሪያቸው በአለም ፊት ነቃፊ የሌለበት መሆን እንዳለበት በአደራ በተቀበሉት ሀብት ፤ንብረት ትዳር ታማኝ መሆን እንዳለባቸው ለራሳቸውና ለሌሎች በክርስቶስ በሆነ መንፈሳዊ እድገት ማድረግ እንደሚያስፈልግ መረዳት እንዳለባቸው እናምናለን፡፡

መንፈሳዊ ስርዓቶች፡- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሁለት ስርአቶችን እንደሰጠ እናምናለን፡፡ ጥምቀትና የጌታ እራት፡፡ ክርስቲያናዊ ጥምቀት በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም አማኝ በውሃ ውስጥ መጥለቅ እንደሆነ እናናለን፡፡ የጌታ እራት በሞቱ መታሰቢያ እንደሆነ በክርስቶስ የተሰጠ ስርዓቶች እንደሆነ እናምናለን፡፡ እነዚህ ሁለቱ ስርአቶች ክርስቶስ ዳግመኛ እስከሚመለስ ድረስ መታሰቢያ እና መደረግ እንዳለባቸው እናምናለን፡፡

የመጨረሻ ዘመን፡- ጌታ ኢየሱስ በግልፅ በአካል ወደ ምድር ተመልሶ እንደሚመታና በመንግስቱ መቋቋም እናናለን፡፡ ትንሳኤ በመጨረሻው ፍርድ ፤በፃድቃን የዘላለም ደስታ እና መጨረሻ ለሌለው የሀጢአተኞች ሰዎች ስቃይ እናምናለን፡፡

የዒላማ መግለጫ

የፉል ፔንቴከስታል ቤተክርስቲያን ከወንጌል ለመድረስ ትኩረት ሰጥታ ለመስራት የመጨረሻው የሰዎች ዓይነት የሚከተሉት ናቸው፡-

አእምሮ ህሙማን

ጎዳና ተዳዳሪዎች

ሴተኛ አዳሪዎች

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች