🔊 ሬማ ዴይሊ/ሬማ በየእለቱ
ዕለታዊ የእግዚአብሔር እንጀራ
ቀን 2/1/2014 እለተ ዕሁድ
የፀና ግምብ ውስጥ የገባ ሰው ዋስትና
የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል። መጽሐፈ ምሳሌ 18 : 10
✦ጥንታዊያን ማህሰበረሰቦች ሐገራቸውን ከወራሪ ሃይል ለመጠበቅ እና ሐገራቸውን ለማስከበር መላ ከተማውን በአራቱም የከተማ ማዕዘናት ከትላላቅ ድንጋይ በተሰራ ቅጥር ይከልሉ ነበር። ምክንያቱም አንድ ሐገር ቅጥር ከሌላት ደካማና ለጠላት ጥቃት በቀላሉ የተጋለጠች ትሆናለችና።
✦ቅጥር ያላት ከተማ ዋስትና ያላት ከተማ ትሆናለች።የአንድ ከተማ ጥንካሬና ማስፈራት በግምቧ ጥንካሬና ፅናት ላይ የተመሰረተ ነበር። ቅጥር ባላት ከተማ ውስጥ የሚኖር ሰው በውጫዊ ነገሮች አይረበሽም፣የጠላት ጥቃትም አያገኘውም። ቅጥር ውስጥ ያለ ህዝብ ከቅጥር ውጪ ባሉ ድምፆችና ሁከቶች አይወሰድም።
✦በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን ስንድን የኛ ቅጥር የእግዚአብሔር ስም ነው።
ስሙ የፀና ግምብ ነው። ይህ ማለት የማይፈርስ፣የማይናድ ግምብ ነው ማለት ነው።ሃሌሉያ!!
በክርስቶስ ወይም (IN CHRIST) ስንሆን ልክ ቅጥር ያላት ከተማ ውስጥ እንደገባ ሰው እኛም ስሙ ውስጥ ገብተናል።ከዚህም የተነሳ የሚያሰጋን የለም።የትኛውም የጠላት ሃይል የእግዚአብሔርን ስም አሸንፎ ወደኛ ሊደርስ አይችልም።
ሰይጣንና አለም አንተ ጋር ከመድረሳቸው በፊት የሚያነጋግሩት የፀና ግምብ አለ።እሱም ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነው የኢየሱስ ስም ነው።
✦እንደ አማኝ በእግዚአብሔር ስም ስላለን ስፍራና ስልጣን(POSITION AND AUTHORITY) የነቃ አስተሳሰብና መረዳት ሊኖረን ይገባል።
አለበለዚያ ያልገባንን መንፈሳዊ ህይወት በፍጹም መኖርም መለማመድ አንችልም።
የእግዚአብሔር ስም ዘላለማዊ የሆነ ዋስትና ነው።ወደዚህ ፅኑ ግምብ የገባ ሰው በህይወቱ ያሉ ፍርሃት፣ስጋት፣ሐዘን፣ ብቸኝነት፣ተስፋ መቁረጥ ያከትምላቸዋል።
✦የዛሬው ቀን በእምነትና በመንፈስ የኢየሱስን የስሙን ስልጣን ተረድተን ሁለንተናችንን ለስሙ የምናስገዛበት ነው። እንዲሁም የተሰጠንን ባለስልጣን ስም =ኢየሱስ= በአንደበታችን የምናውጅበት፣የምንሸሸግበት ነው። ምክንያቱም ፃድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።ወይም በሰላም ይኖራል።
”ከፍ ከፍ ”ይላል የሚለው የዕብራይስጥ ትርጉም ደህንነትና ሰላም ማግኘትን ያመለክታል።
The name of the LORD [is] a strong tower: the righteous runneth into it, and is safe. Proverbs 18 : 10
✦የኢየሱስ ስም የመለኮት ሃይል ጥቅል (Package)ነው።ስሙ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ባለስልጣን ነው። ስሙን ስጠሩ ስሙ ይገለጣል። ለእናንተ መልካም ውጤት ያመጣል። ስሙን ተደገፉ ስሙን እንደገፍ፣ ስሙን እመኑ፣ስሙን ተጠቀሙ፣ስሙን አክብሩ። ስሙ የፀና ግምብ ነው።
በምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ይህን መልዕክት እያነበባችሁ የኢየሱስን የስሙን ታላቅነት አስቡ። ከስሙ የሚበልጥ ምንም አይነት ነገር በምድርም ሆነ በሰማይ የለም።
ስሙ የፀና ግምብ ነው። ስሙ ውስጥ በእምነት ተሸሸጉ።ስሙ ዋስትናችን ነው።
ሻሎም!!
🕊🌻በ2014 ለሚመጡት 364 ቀናቶች ዕለታዊ የእግዚአብሔር እንጀራ ወደናንተ እንዲደርስ እግዚአብሔር ቃል ይሰጠኝ ዘንድ አጥብቃችሁ ፀልዩልኝ።
🌻ከዚህ ቀደም በየእለቱ ሲቀርቡላችሁ የነበሩትን ዴይሊ ሬማ(ሬማ በየእለቱ) ወደኋላ ሄዳችሁ ለእናንተም ለወዳጆቻችሁም ታካፍሏቸው ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ።
የእግዚአብሔር ቃል ህያውና የሚሰራ ነው!!
©በነቢይ መሳይ አለማየሁ
👇👇👇👇👇👇 👇👇👇
@FullPentecostalChurch
@FullPentecostalChurch
@FullPentecostalChurch
